Job Overview
በውጭ አገር ለመሄድ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ማወቅ አለባቸው። አጭበርባሪዎች ሊያሳቸው የሚችሉ ነገሮችን ከማወቅ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ምክሮች እና አስተ警示 ይቀርባሉ።
Key Details
- Location: ውጭ አገር
- Salary: ከፍተኛ ደመወዝ (የሚታወቀው አይደለም)
- Deadline: አይተነተና
- Experience: ያለ ምንም ትምህርት ወይም ክህሎት (የሚታወቀው አይደለም)
Job Requirements & Description
ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ” ውጭ አገር እንልካለን ” በሚሉ አጭበርባሪዎች ያላችሁን ፣ ተበድራችሁ የመጣችሁትን እንዳታጡ ጥንቃቄ አድርጉ።
ያስተውሉ ፦
- ንግድ ፍቃድና ቢሮ ስላላቸው ብቻ አትመኗቸው
አንዳንዶቹ ለጥቂት ወራት ቢሮ ተከራይተውና የሰው ፍቃድ ወይም የራሳቸውን ፍቃድ ይዘው የብዙዎችን ገንዘብ ሰብስበው ይሰወራሉ።
ስለሆነም የድርጅቶቹን ማንነት በደምብ #አጣሩ - ገንዘብ በባንክም ቢሆን በጭራሽ እንዳታስገቡ በካሽ እጅ በእጅ ስጡን ካሉ በፍጹም እንዳታምኗቸው
” ቪዛ ተመትቷል” በሚል ማታለያ በባንክ አካውንታቸው ብር እንድታስገቡ ካደረጉ በኋላ ስልካቸውን ዘግተው የሚጠፉ አሉ አልያም
በካሽ እጅ በእጅ ስጡን ካሉ ገንዘባችሁን ይዘው ለመሰወር ብቻ ነው።
በሕጋዊ መንገድ ሳትሄዴ ምንም ክፍያ አትፈጽሙ - የቲክቶክ፣ በፌስቡክ ፣ ቴሌግራም ወይም ሌሎች ሚዲያዎች ላይ የሚተላለፉ የተጋነኑ ማስታወቂያዎችን አትመኑ።
- በአጭር ቀን እንልካችኋለን
- ያለ ስልጠና እንልካችኋለን
- ያለ ምንም ትምህርት እና ክህሎት ትሄዳላችሁ
- ከፍተኛ ደመወዝ ታገኛላችሁ
የሚሉ ማባበያዎች የሌቦች ወጥመድ ናቸው
- ታዋቂ ሰዎችን ታዋቂ ብቻ ስለሆኑ አትመኑ። እነሱ አሉ ማለት ብቻ እውነት ነው ማለት አይደለም
አርቲስቶች ወይም ታዋቂ ሰዎች ስለተከፈላቸው ብቻ ማስታወቂያ ሊሰሩ ይችላሉ፤ የእነሱ መኖር የድርጅቱን ታማኝነት አያረጋግጥም።
ስለዚህ ስለ ድርጅቱ በደምብ #አጣሩ - ዋና ፓስፖርታችሁን አሳልፋችሁ አትስጡ
” ቪዛ ለማስመታት ” ወይም ” ሂደት ለመጀመር ” በሚል ሰበብ ዋና ፓስፖርታችሁን ተቀብለው ለወራት ሊያንገላቷችሁ እና
ሊያስፈራሯችሁ ይችላሉ። የፓስፖርት ፎቶ ኮፒ ብቻ መስጠት ይበቃል፤ ዋናው ፓስፖርት ጉዞው ተረጋግጦ አሻራ እስኪሰጥ ድረስ በእጅዎ
መቆየት አለበት
How to Apply
በተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይጎብኙ፡ https://effoysira.com/